💔 ሱሶች በጤና ላይ የሚያደርሱት ጉዳት 💔

💔 ሱሶች በጤና ላይ የሚያደርሱት ጉዳት 💔

Aug 30, 2025

አካላዊ ጉዳት
የአልኮል ሱሶች: የጉበት መጎዳት ፣ የልብ ህመሞች፣ የሆድና የጨጓራ ችግሮች፣ የአንጎል ጉዳት፣ የካንሰር አጋላጭነት፣ የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ።
ሲጋራ ሱሶች: የሳንባ በሽታዎች (ካንሰርን ጨምሮ)፣ የልብና የደም ዝውውር ችግሮች፣ የአፍና የጥርስ በሽታዎች፣ የቆዳ መሸብሸብ።
የአደንዛዥ እጾች ሱሶች: ለሞት የመጋለጥ አጋላጭነት ፣ የሰውነት ክፍሎች መጎዳት፣ የተላላፊ በሽታዎች ፣ የአእምሮና የስነ-ልቦና መቃወስ።

ለስነ-ልቦና ጤንነት:
የጭንቀትና የድብርት መጨመር: የስሜት አለመረጋጋት፣ የመንፈስ ጭንቀት።
የባህሪ ለውጥ: ቁጣ፣ ብስጭት፣ ራስን መቆጣጠር አለመቻል፣ የማስታወስና የትኩረት ችግር።
የማህበራዊ ግንኙነት መበላሸት: ከቤተሰብና ከጓደኞች መራራቅ።
የራስን ማንነት ማጣት: ህይወት ሱሱን ብቻ ማዕከል ታደርጋለች።

✨ መፍትሄው ምንድን ነው? ✨

መፀፀትና ወደ አላህ መመለስ (ተውበት ማረግ): ለአላህ መፀፀትና ምህረትን መጠየቅ።

የቤተሰብና የጓደኞች ድጋፍ: የሚወዷቸው ሰዎች የድጋፍ አካል መሆን አለባቸው። የአላህን እርዳታ መጠየቅ: ዱአ ማድረግ፣ ቁርአን መቅራትና የሃይማኖት ትምህርቶችን መከተል።
የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ: ጤናማ ምግብ መመገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የትርፍ ጊዜ ስራዎችን መፈለግ እና ሱሱ ወደሚያስገባን ሁኔታ እንዳንገባ መጠንቀቅ።

"ሱሶች የህይወት ጥራትን የሚያበላሹና አጥፊ ናቸው። ጤናማና አላህ በወደደው መልኩ የምትኖር ህይወት ለመምራት፣ ከሱሶች ራስህን ጠብቅ! ሱስን ከተጋፈጥክም፣ እርዳታ ለመጠየቅ አታመነታ!"

❤️ኢፋዳ ጤና-ለጤናማ ማህበረሰብ❤️
አዘጋጅ :- ሚፍታህ
አልሙሀጂሪን ሀድራ